አዲስ ፋና ሸቀጣ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር ለአክሲዮን ማህበሩ ድርጅታዊ መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ጥናት አገልግሎት የሚሰጡ ብቁ አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ድርጅታዊ መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ማስጠናት ይፈልጋል፡፡
የአገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ፋና ሸቀጣ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር ለአክሲዮን ማህበሩ ድርጅታዊ መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ጥናት አገልግሎት የሚሰጡ ብቁ አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ድርጅታዊ መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ማስጠናት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት በጨረታው መሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተቋም በጨረታው መሣተፍ ይችላል፡፡
- በመስኩ የሙያ ፈቃድ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርቲፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታክስ ክሊራንስ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የሰ/ሀ/ል/አስ/መምሪያ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond) የሚወዳደሩበትን የሥራ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አሥር ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት አለባቸው፤
- ጨረታው በወጣ በአሥራ አንደኛው ቀን ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ በአክሲዮን ማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፤
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-
0922590391 ወይም 0911414352 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ ፋና ሸቀጣ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበሩ
