Tender Detail

Tender Details

  • Company የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address ሳሪስ ከነጋ ቦንገር ወደ ብሄረጽጌ በሚወስደው መንገድ በላብያጆ ገባ ብሎ ባለው የኮብልስቶን መንገድ ትንሽ ገባ እንዳሉ ወደቀኝ በመጀመሪያ መታጠፊያ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-66-43-15-54
  • Website
  • Deadline23 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-23 00:00:00
  • Categories Machinery , Furniture , Electronics Materials , Used Items , Kitchen Materials

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ንብረት የሆኑትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ጠረጴዛና ወንበሮች፣ የስፌት ማሽኖች፣ የሽመና ማሽን፣ ፍሪጅ፣ ስቶቭ እና የእንጀራ ምጣድ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ንብረት የሆኑትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ጠረጴዛና ወንበሮች፣ የስፌት ማሽኖች፣ የሽመና ማሽን፣ ፍሪጅ፣ ስቶቭ እና የእንጀራ ምጣድ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን 6/10/2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 16/10/2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት 2፡30 እስከ 09:30 ሰዓት በመጨረሻው ቀን በ16/10/2017 እስከ ጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ በብርሃን ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ ግምገማ ውጤት እንደፀደቀ ይመላስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎች ዝርዝር ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በድርጅቱ የጨረታ ሳጥን ውስጥ 16/10/2017 ዓ.ም. እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ አድርገው በ5 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስገቡት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16/10/2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ረፋዱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ ረፋዱ 5፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የጨረታ ሳጠኑ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
  9.  ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-66-43-15-54/09-13-04-51-18/ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡- ሳሪስ ከነጋ ቦንገር ወደ ብሄረጽጌ በሚወስደው መንገድ በላብያጆ ገባ ብሎ ባለው የኮብልስቶን መንገድ ትንሽ ገባ እንዳሉ ወደቀኝ በመጀመሪያ መታጠፊያ

 

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት

 

Save Tender