የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ካፖርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
(ጨረታ ቁጥር ኢአጽ/ግንአዳ/019/2017)
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ካፖርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ ፣ የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ብር 40,000.00 (አርባ ሺ) የጨረታ መስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በዚሁ እለት ማለትም ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8:30 ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
