የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ሀምሌ 01/2017 እስከ ኅዳር 30/2018 ድረስ ለ5 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት ሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅቶች እንዲሁም ጥሬ እህል፣ የማገዶ እንጨት፣ የማጣፈጫ ሸቀ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 2
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ሀምሌ 01/2017 እስከ ኅዳር 30/2018 ድረስ ለ5 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት ሚውል
የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅቶች እንዲሁም ጥሬ እህል፣ የማገዶ እንጨት፣ የማጣፈጫ ሸቀጣሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች ማሟላት አለባቸው።
- በንግድ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይነት (TIN NO) ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ፣ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
- ጥሬ እህል ለማቅረብ ለሚወዳደሩ የእህሉን ናሙና እና የሚወዳደሩበትን አይነት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡትን ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም።
- አሸናፊው አሸነፊነቱ ከታወቀበት ቀን አንስቶ በ3 ቀናት ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጁ ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ በማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ የማሟላት ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደ/ም/ሸ/ዞን/ገ/ኢ/ልማት/ትብብር ፅ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-341-1190/011341-00-23
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ
