የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን የጽኅፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን የጽኅፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በመስኩ የተሰመሩ ነጋዴዎች አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾቹ ማሟላት ያላባቸው ነገሮች :-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አምቦ በሚገኘው ከዩንየኑ ገበያ ክፍል በ500 ብር መግዛት ይችላሉ።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ወድያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለ5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ6ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል። 6ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች /ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የማቅረብያ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 09 13 37 94 35፣ 011 236 3399 ይጠቀሙ፣
የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን
