Tender Detail

Tender Details

  • Company Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ወርቁ ሰፈር (ውሃ ልማት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ መስጊዱ እካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 17 51 51
  • Websitehttps://www.dce-et.com/
  • Deadline27 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-27 00:00:00
  • Categories Building Construction , System Supply And Installation

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ Supply and fix projection system ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-DCE/SF/111/2025

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ Supply and fix projection system ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

1

Supply and fix projection system

ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግንባታ

DCE/SF/111/

2025

ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት

ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት

200,000.00

 

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሃገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ... ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው የስራ ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 011-4-40-34-33/34

ማዞሪያ፡- 011-4-42-22-70/71/72

E-mail አድራሻ፡- info@dce-et.com 

የድረ-ገፅ አድራሻ:- www.dce-et.com 

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender