በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ነገሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን ፃ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን
ሎት 3 የህትመት ውጤቶች
ሎት 4 የመኪና ጎማ እና የግብርና ግብዓቶችን በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን
ከሚወዳደሩት ስራ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸዉ ፈቃድ አንድ አመት የሞላዉ ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer ldentificatin Number) ያላቸዉ፣
- በግዥ አፈጻጸም መመሪያዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ዉጭ የገዥዉ መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፤
- የሚገዙ የእቃዎች ን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናዉን የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታዉ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን 100 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃወ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀነ 4:30 ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- በዚህ የጨረታ ማስታዎቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 ተግባራዊ ይደረጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የፃ/ወ/ገ/ፅ/ቤት
