የምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከሐምሌ 01/2017 እስከ ታህሳስ 30/2017 ድረስ ለ6 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ለህግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት ፡ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1
የምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከሐምሌ 01/2017 እስከ ታህሳስ 30/2017 ድረስ ለ6 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ለህግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት ፡ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆኑ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው።
- በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት። የግብር ከፋይነት (TIN NO) ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡት ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይችልም፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ በ3 ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጁ ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው:
- ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ በማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበራት ወይም ግለሰብ የማሟላት ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ምዕ/ሸ/ዞን/ገ/ኢ/ልማት/ትብብር ፅ/ቤት
ለበለጠመረጃ ስልክ ቁጥር:- 011-236-20-82/ 011341-00-23
የምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች ጽ/ቤት
