የኤም.ሲ. ኤምኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ያህል በሚቆይ የኮንትራት ውል መሠረት ለሆስፒታሉ አቅርቦት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪከና የቧንቧ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
MCM Comprehensive Specialized Hospital (ኤም.ሲ.ኤም ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል /ኮሪያ/ ሆስፒታል)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኤም.ሲ. ኤምኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ያህል በሚቆይ የኮንትራት ውል መሠረት ለሆስፒታሉ አቅርቦት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪከና የቧንቧ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 – የጽህፈት ዕቃዎች፣
- ሎት 2 - የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3 - የኤሌክትሪክና የቧንቧ ዕቃዎች፣
ማንኛውም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተእታ (VAT) ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ደብዳቤ የተረጋገጠ ቼክሊስት ኦፍ ክሬዲት ወይም የባንክ ዋስትና (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ገርጂ በሚገኘው በሆስፒታላችን ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ አኑረው 2 (ሁለት) ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ በሚል ተለይቶ በግልጽ ፖስታው ላይ በመጻፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው 15ተኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ በ8፡15 ሰዓት ታሽጐ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ቤተ-መጻህፍት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ላይ ይገለጻል፡፡
- የምርት ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች በሆስፒታሉ አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 10% (CPO) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር የውል ስምምነት ይፈጽማሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ገርጂ
ስልክ ቁጥር፡- 011-6-29-54-22/23/24
011-6-29-20-91 ፋክስ 011-6-29-27-95
ኤም. ሲ . ኤም ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል /ኮሪያ/ ሆስፒታል
