Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ቋሚ እና አላቂ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ቋሚ እና አላቂ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል። ስለሆነም ያገለገሉ ንብረቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

1. ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበሮች ፣ 2. ያገለገሉ የካፌ ጠረጴዛ ፣ 3. ያገለገሉ የእንጨት ሸልፍ ፣ 4. ያገለገሉ ኮት መስቀያ ፣ 5. አዲስ የመፀዳጃ ቤት ሲንክ ፣ 6. ያገለገሉ የመስታወት ሸልፍ ፣ 7. ያገለገሉ ማከፋፈያ ፣ 8. ያገለገሉ የመስመር የስልክ ቀፎ ፣ 9. ያገለገሉ የወረቀት መብሻ ትልቁ ፣ 10. ያገለገሉ ስቴፕለር መምቻ ትንሹ፣ 11. ያገለገሉ ስቴፕለር መምቻ ትልቁ ፣ 12. ያገለገሉ ስቴፕለር መምቻ መካከለኛ ፣ 13. ያገለገሉ የእጅ ባትሪ ትልቁ ፣ 14. ያገለገሉ የእጅ ባትሪ ትንሹ ፣ 15. የመኪና ልብስ ያገለገለ ፣ 16. ያገለገለ ፕላስቲክ ወንበር፣ 17. ያገለገለ የቆሻሻ ቅርጫት ፣ 18. ያገለገለ ፒፒሲ ባለ20 ፤ 19. ያገለገለ የውሃ ማጣሪያ፣ 20. ያገለገለ ካውንተር ፣ 21. ያገለገለ ትራንስፓረንሲ ብርሃን ማስተላለፊያ የጣሪያ ልብስ ፣ 22. ያገለገለ ፍሪጅ /indesit/ ፣ 23. ያገለገለ ጃንቦ ድራፍት መጠጫ ብርጭቆ ፣ 24. ያገለገለ የሲንግል ድራፍት መጠጫ ብርጭቆ ፣ 25 ያገለገሉ የተለያዩ የቢራ ጠርሙስ ከነሳጥናቸው ፣ 26. ያገለገሉ የተለያዩ የቢራ ጠርሙስ ማስቀመጫ ሳጥኖች ፣ 27. ያገለገሉ የተለያዩ የለስላሳ ጠርሙስ ማስቀመጫ ሳጥኖች ፣ 28. ያገለገሉ የአምቦ ውሃ ጠረሙስ ከነሳጥናቸው ፣ 29. ያገለገሉ የአምቦ ውሃ ጠርሙስ ማስቀመጫ ሳጥኖች ፣ 30.ያገለገሉ የተለያዩ የአረቄ ጠርሙስ ከነሳጥኑ ፣ 31. ያገለገሉ የወይን ጠጅ ጠርሙስ ከነሳጥኑ ናቸው።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፤ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የሰጠው ዋጋ በሚሞላው አምድ ስር ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ ጽፈው ከፈረሙ በኋላ በፖስታ አሽገው በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ ወይም ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 705 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

  1. ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሰነዱን ገዝቶ መውሰድና የሚወገዱ እቃዎች ላይ በጨረታ በመግዛት መሳተፍ ይችላል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ ወይም ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በሚገኘው መርካቶ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ታሽጎ በመ/ቤታችን በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት ለእያንዳንዱ ቁጥር ለተቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (Addis Ababa City Administration Revenues Bureau Merkato No.2 M/T/P/Branch Office) ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ፖስታ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ቀናት እስከ ጠዋቱ 04፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  6. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  7. ንብረቱ የሚሸጠው አሁን ባለበት ሁኔታ ይሆናል።
  8. ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ 7ኛ አካባቢ ድሬ ህንጻ ጎን ባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ባለው ስቶር ነው።
  9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ 011-2-76-98-62-/011-2-73-27-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender