በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1፡- የምግብ ግብዓት ለአንድ አመት ውል የሚፈረም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የእቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/ቁ/04/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡- ሎት 1፡- የምግብ ግብዓት ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ለ2018 በጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፤
- ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዝ
- ሎት 1- የምግብ ግብዓት ግዥ ለአንድ አመት ውል የሚፈርም ለ2018 በጀት አመት የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO): ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ የሚያስይዝ፡፡
- ተጫራቾች ናሙናዎቻቸውን የራሳቸውን መለያ ኮዳቸውን ሰጥተው ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት (የራሱ ስቶክ) ያለውና እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ክ 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን፡፡
በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111112056 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል
