ድርጅታችን ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት አዳማ በሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለከባድ ተሽከርካሪዎች መጠገኛና ማቆሚያ ቦታ የሚውል ጋራዥ ግቢ ውስጥ እና ጋራዥ አካባቢ የሚገኘውን ቀይ አሸዋ ፣ ገረጋንቲ እና ማሽነሪ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን በመፈለጉ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/አቅ/017/17
ድርጅታችን ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት አዳማ በሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለከባድ ተሽከርካሪዎች መጠገኛና ማቆሚያ ቦታ የሚውል ጋራዥ ግቢ ውስጥ እና ጋራዥ አካባቢ የሚገኘውን ቀይ አሸዋ ፣ ገረጋንቲ እና ማሽነሪ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን በመፈለጉ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ስመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራታቸው የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገቢዎች ሚኒስቴር የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝር መሠረት በማድረግ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ይከፈታል፤ ነገር ግን የመከፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ለቀይ አሸዋ እና ገረጋንቲ (ሰሌክት ማቴሪያል) ግብኣትና ማሽነሪ አቅርቦት የሚያስፈልገውን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር /ከነቫቱ/ በማዘጋጀት በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ለዚህ አገልግሎት እንዲውል በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ደረጃ 6 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ (GC-6) እና ከዚያ በላይ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልጽ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአቅርቦት /ፋ/ማ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቀረበውን የዕቃ ዝርዝር መሠረት በማድረግ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአቅ/ፋ/ማ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም ከጨረታው ሰነድ ጋር በማስያዝ/ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ (ፐርፎርማንስ ቦንድ) የአጠቃላይ ዋጋውን 10% በሲፒኦ በማስያዝ ውል ገብቶ ሥራውን መጀመር አለባቸው፤
- አሸናፊ ተጫራች በገባው ውል መሰረት ሥራውን ባይጀምር ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-በስልክ ቁጥር 011 439 00 75 / 011 439 10 27 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው፤
ዕለት ደረሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
