የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የዋናው መ/ቤት የአስፓልት እና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) ጽዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/27/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የዋናው መ/ቤት የአስፓልት እና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) ጽዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የአስፓልት እና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) ጽዳት አገልግሎት ግዥ የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/27/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ሎት |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የአስፓልት እና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) ፅዳት አገልግሎት |
10,000.00 (አስር ሺህ ብር) |
ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
