Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ጎንደር ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2112828
  • Website
  • Deadline21 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-21 00:00:00
  • Categories Building Construction

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጎንደር ከተማ የሚገኙትን የክላስተር ማዕከላት ባሉት ሶስት ሼድ የውሃ ፍሳሽ የጥገና ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል።

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጎንደር ከተማ የሚገኙትን የክላስተር ማዕከላት ባሉት ሶስት ሼድ የውሃ ፍሳሽ የጥገና ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በጥገና ሥራው መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. ደረጃ 8 GC/BC እና በላይ የሆነ ማንኛውም ተቋራጭ፤
  2. ሕጋዊ በዘመኑ በ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባም ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. በ2017 ዓ.ም የሥራ ዘመን የታደሰ መሆኑን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ሆኖ በክልል ንግድ ፈቃድ ያወጡ ከክልል ከተማ መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም የዞን መምሪያ ከፌዴራል ንግድ ፈቃድ ያወጡ ከፈዴራል ከተማና መሰረተ ልማት ኮንስትራከሽን ሚኒስቴር ያወጡ
  4. ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልገውን ማቴሪያል እና የሰው ኃይል ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጎንደር ከተማ አማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ጠ/አገ/ቡድን ቢሮ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ ተከታታይ ቀናት ሆኖ ቅዳሜ ግማሽ ቀን እስከ 6፡30 ሰዓት የሥራ ቀን መሆኑ ታሳቢ ተደርጎ የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% የማያንስ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ሲፒኦ በአማራ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ስም ተሠርቶ የሚቀርብ ሲሆን፤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በአብክመ ኢፓልኮ ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ጠ/አገ/ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅ/ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ጠ/አገ/ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ላይ ካረፈ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መስፈርትና የሥራ ዝርዝር መሰረት ዋጋ መሙላት የሚኖርበት ሲሆን በተቀመጠው የሥራ ዝርዝር መሰረት ዋጋ ያለመሙላት በራስ የዋጋ መሙያ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ፣ ስርዝ ድልዝ መኖር አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. አሽናፊው ከተገለጸ በኋላ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የማያንስ በአማራ ኢንዲስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ተሠርቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  9. አሸናፊው ከተገለጸ በኋላ ካሎት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ ካልያስያዘ እና ውለታ ካልፈፀመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል፤
  10. ጽ/ቤቱ ጥገና የሚከናወንበትን ሳይት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን በኋላ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 -9:00 ስለሚያስጎበኝ ማየት የምትፈልጉ ተገኝታችሁ ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

“ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-2112828 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ"

 

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender