የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር (ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/24/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ ፣ የቫት ተመዝጋቢ፤ ቲን እና ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋጋ ለ90 (ዘጠና) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ-
ስልክ ቁጥር 011470-90-95 ወይም 0114-423608
ፋክስ 0114-421312
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
