Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ የኬላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2017 ዓም በጀት ዓመት ከወ/ሮ ካለች ታደለ ሱቅ እስከ አቶ አሰፋ ገ/እግዚሐብሄር ቤት ድረስ 1 ኪ.ሜ የሚሸፍን ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ የኬላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2017 ዓም በጀት ዓመት ከወ/ሮ ካለች ታደለ ሱቅ እስከ አቶ አሰፋ ገ/እግዚሐብሄር ቤት ድረስ 1 ኪ.ሜ የሚሸፍን ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ተወዳዳሪዎች በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፍቃድ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው። ተወዳዳሪዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በአካል በመቅረብ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው ቀን ይሆናል። ነገር ግን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን ጨምሮ ከሆነ በቀጣይ ቀን ልክ ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በ8፡00 ሰዓት በአካል በመገኘት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender