Tender Detail

Tender Details

  • Company የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0467760362
  • Website
  • Deadline12 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-12 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም በጨ/ዙ/ወ ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውል የጽ/መሣሪያና የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም በጨ/ዙ/ወ ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውል የጽ/መሣሪያና የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚያስፈልጋቸው፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የነጋዴ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  4. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት online /ድረ-ገጽ/ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፤
  5. የዋጋ ማቅረቢያ በእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  7. ተጫራቾች የመልካም ሥራ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  8. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ጨንቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርበታል፡፡
  9. ቫት በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ካልተገለጸ እንደተገለፀ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  10. የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ግዴታ አለበት።
  11. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  12. ጨረታ አሸናፊ ድርጅት ውል ከመግባቱ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
  13. የማስጫኛና የማውረጃ ወጪዎችን በአሸናፊው ድርጅት ይሸፈናል፡፡
  14. የጨረታ ሰነድ ጨንቻ ወረዳ ዙ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
  16. የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሸጎ ከቀኑ በ9:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ስለሆነም 16 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  17. የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  18. የጨረታው ማስከበሪያ /Bid bond/ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ በጥሬ ገንዘብ የምንቀበል መሆኑን እያሳሰብን በየሎቱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  19. በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀው ዋጋ ከውል ጊዜ ጀምሮ ለዘጠና ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
  20. አሸናፊው ድርጅት ውል ለመግባት ሲመጣ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ የሚችል የምትችል መሆን አለበት።

ማሳሰቢያ፡-

  1. በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  2. የበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 046-7-76-03-62/ 09-10-11-84-27
  3. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

Save Tender