Tender Detail

Tender Details


አዋሽ ባንክ አ.ማ ሲጠቀምባቸው የነበረውን 19 ተሽከርካሪዎች በሎት (1) እና በሎት (2) የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ንብረቶችን (ጄኔሬተሮች፣ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ እስካነር፣ የውሃ ማጣሪያ፣ መፈተሻ ማሽን፣ የሂሳብ መደመሪያ፣ ታይፕራይተር፣ የሙቀት መለኪያ፣ የብር መቁጠሪያ ማሽን፣ የዶላር መፈተሻ ማሽን፣ ፎቶ ኮፒ፣ ፋክስ፣ ፍሪጅ፣ ቴሌቪዥን፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ ኤቲ ኤም ሼልተር፣ የመጽሐፍ መደርደሪያ፣ ፋይሊንግና ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት፣ የኮት መስቀያ፣ መጋረጃ፣ ፍራሽ ካውንተር፣ እምነበረድ፣ የጥበቃ ቤት፣ እስታፕላይዘር፣ ባትሪ፣ ዩፒኤስ፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ያገለገሉ ጐማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫ የእንጨት ሣጥኖች፣ ንቃይ ቆርቆሮዎች እና የተለያዩ የማስታወቂያ ምልክቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


 

ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ

 

አዋሽ ባንክ አ.ማ ሲጠቀምባቸው የነበረውን 19 ተሽከርካሪዎች በሎት (1) እና በሎት (2) የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ንብረቶችን (ጄኔሬተሮች፣ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ እስካነር፣ የውሃ ማጣሪያ፣ መፈተሻ ማሽን፣ የሂሳብ መደመሪያ፣ ታይፕራይተር፣ የሙቀት መለኪያ፣ የብር መቁጠሪያ ማሽን፣ የዶላር መፈተሻ ማሽን፣ ፎቶ ኮፒ፣ ፋክስ፣ ፍሪጅ፣ ቴሌቪዥን፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ ኤቲ ኤም ሼልተር፣ የመጽሐፍ መደርደሪያ፣ ፋይሊንግና ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት፣ የኮት መስቀያ፣ መጋረጃ፣ ፍራሽ ካውንተር፣ እምነበረድ፣ የጥበቃ ቤት፣ እስታፕላይዘር፣ ባትሪ፣ ዩፒኤስ፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ያገለገሉ ጐማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫ የእንጨት ሣጥኖች፣ ንቃይ ቆርቆሮዎች እና የተለያዩ የማስታወቂያ ምልክቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡-

  1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-101 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣
  2. እያንዳንዱ ተጫራች (በሎት 1) ላይ ለተገለጹት ተሽከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣
  3. እያንዳንዱ ተጫራች (በሎት 2) ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንከ አክስዮን ማህበር ስም አስርቶ ማስገባት ይኖርበታል፤
  4. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
  5. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15%፣ ለተሽከርካሪዎቹ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን ይከፍላል፣
  6. ንብረቶቹን እሸዋ ሜዳ እና ጃክሮስ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ባንኩ እያስገነባ በሚገኘው ሕንጻ ቅጥር ግቢ በአካል ቀርቦ በጨረታው ሰነድ ላይበወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፣
  7. ጨረታው ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ከፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣
  8. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  10. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115-30-30-14/0115-30-30-26/0115-57-68-15 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

አዋሽ ባንክ አ.ማ

 

Save Tender