በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ የተለያዩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ የጨርቅ ሸራ መጠኑ 9*11 ሜትር እና ካቦ 12 ሚሊ ሜትር በተቀመጠው መመሪያና ግዴታዎች መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ጥገና ዘርፍ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፡- ተአጥዘ/ግጨ/03/2017
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ የተለያዩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ የጨርቅ ሸራ መጠኑ 9*11 ሜትር እና ካቦ 12 ሚሊ ሜትር በተቀመጠው መመሪያና ግዴታዎች መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ማንኛውም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች መጫረት ይችላል፡፡
- የግዥ ፈፃሚ አካል ስም:- በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ
- የዕቃው ዓይነት፡-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች -
- አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒውን በማቅረብ ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ኮፒውን በማቅረብ ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በመንግሥት መስሪያቤቶች በዕቃ አቅራቢነት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
- የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሠነድ ከተከፈተ በኋላ በቴክኒክ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች የተወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት በክምችት እንዳላቸው ይህንን ዕቃ ለማየት ለሚመጡ የኮሚቴ አባላት ማሳየት ይኖርባቸዋል። በተለያዩ ምከንያት ሳያሳዩ ቢቀሩ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቃሊቲ የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ በሚገኘው መስሪያ ቤት የግዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ዕቃ የአጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል (CPO) ሲዘጋጅ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደር ጥገና ዘርፍ ስም መዘጋጀት አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን፡- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀናት እንዲሁም የዕረፍት ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ሳይገኝ ቢቀር የጨረታው መከፈት ሂደት አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የተለያዩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ የጨርቅ ሸራ መጠኑ 9*11 ሜትር እና ካቦ 12 ሚሊ ሜትር የሚጫረቱበትን ዋጋ በግልፅ እንዲሁም በሚታይና ግልፅ በሆነ መንገድ ከስርዝ ድልዝ በፀዳ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ አንድ ዋና (original) እና አንድ ቅጂ (copy) ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግና በመፈረም የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ አድራሻ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡30 - 11:00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቃሊቲ በሚገኘው የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡ የጨረታ ሰነዱ ሳጥን ውስጥ ከመግባቱ በፊት መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነድን ሳይገዛ የተጫረተ ማንኛውም ድርጅት ከተገኘ ከጨረታው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ዘርፉ ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ አድራሻ ቃሊቲ ጉምሩክ የባቡር መጨረሻው ጣቢያ ፊት ለፊት ከአዋሽ ባንክ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ ግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ጊቢ ውስጥ ስልክ ቁጥር 011 470 84 77 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ
