Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ (በቁርጥራጭ) መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት የሚወገዱ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የውሃ ቆጣሪ (በስቲል የሚወገድ) የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DCI ቧንቧዎች እና ያገለገሉ ሞተርና ፖምፕ (በካስት የሚወገድ)፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ የተሽከርካሪና የማሽነሪ መለዋወጫዎች፣ የሽንት ቤት ሳቶፖን ያገለገሉ የህክምና መገልገያ ንብረቶች እና ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ (በቁርጥራጭ) መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት የሚወገዱ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የውሃ ቆጣሪ (በስቲል የሚወገድ) የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DCI ቧንቧዎች እና ያገለገሉ ሞተርና ፖምፕ (በካስት የሚወገድ)፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ የተሽከርካሪና የማሽነሪ መለዋወጫዎች፣ የሽንት ቤት ሳቶፖን ያገለገሉ የህክምና መገልገያ ንብረቶች እና ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት የሚወገዱ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የውሃ ቆጣሪ (በስቲል የሚወገድ)፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DCI ቧንቧዎች እና ያገለገሉ ሞተርና ፖምፕ (በካስት የሚወገድ) ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) እንዲሁም የተለያዩ ያገለገሉ የንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ የሽንት ቤት ሳቶፖን የተሽከርካሪና የማሽነሪ መለዋወጫዎች፣ የህክምና እቃዎች እና ሌሎችም) ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቶች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልግሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል።
  4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎች፣ /በስክራፕ/ በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፤ የተለያዩ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት የሚወገዱ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የውሃ ቆጣሪ (በስቲል የሚወገድ)፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DCI ቧንቧዎች እና ያገለገሉ ሞተርና ፖም (በካስት የሚወገድ) የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፤ ባትሪዎች፤ ፍላፖች፤ ከነመዳሪዎች፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫዎች፣ የሽንት ቤት ሳቶፖን፤ የህከምና መገልገያ እቃዎች እና ሌሎችም የአንዱን መስሪያ ቤት በጥቅል መጫረት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሃላፊነቱን እይወስድም።
  8. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልከ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%) እንዲሁም የተለያዩ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት የሚወገዱ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የውሃ ቆጣሪ (በስቲል የሚወገድ) የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DCI ቧንቧዎች እና ያገለገሉ ሞተርና ፖምፕ (በካስት የሚወገድ) የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ. ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  9. የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።
  11. ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል።
  12. አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፣ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም።
  13. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
  14. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሳይጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።
  15. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል።
  16. ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  17. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም።
  18. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

 

Save Tender