የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል የግቢውን የፅዳት አገልግሎት በአውትሶርስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በአ.ብ.ክ.መ. የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል የግቢውን የፅዳት አገልግሎት በአውትሶርስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን (አገልግሎቱ) ከ200,000 /ሁለት መቶ ጉለት መቶ ሺህ ብር ሺ/ ብር በላይ መሆኑ ሲገመት ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት መስክ ላይ አግባብ ያለው ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከተራ ቁጥር 1- 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸ ዋል።
- የጨረታ ሰነዱ በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነና ለመለየት አሻሚ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም።
- ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ የሚወዳደሩበትን የስራ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት የአገልግሎት ዋጋ የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያገናዘበ መሆን ይኖርበታል።ነገር ግን በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት እና ያለ አግባብ ጨረታውን ለማዛባት መሞከር ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ 1 ወጥ ወይም በ2 ወጥ ፖስታዎች በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር - 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስአት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) በ16ኛው ቀን 3፡20 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ በበአላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 0913 089 057 ወይም 0111 320 741 በመደወል ወይም በአካል በመምጣት ዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 3 ማነጋገር ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡- ሆ/ሉ ምንም አይነት የፅዳት መገልገያ እቃዎች እና የደንብ ልብስ የማያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን። ከላይ የተዘረዘሩት የተጫራቾች መመሪያ ከአጠቃላይ የተጫራቾች ዝርዝር መመሪያዎች በከፊል የተወሰዱ መሆናቸው ይታወቅ።
በአ.ብ.ክ.መ. የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል
