Tender Detail

Tender Details


የፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት እስቶር የሚገኙ አዲስ የግንባታና የኤሌክትሪክ እቃዎች፤ የሻወር ትሪዎች የእጅ እና የእቃ ማጠቢያ ሲንኮች የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች የውሃና የዘይት ቀለሞች እና ሌሎች የማይንቀሳቀሱ እቃዎችና ያገለገሉ የእጅ መሳሪያዎች እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ቅ/3/ን/ማስ/ግ/ጨ/ሽያጭ 02/2017 ዓ.ም

 

የፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት እስቶር የሚገኙ አዲስ የግንባታና የኤሌክትሪክ እቃዎች፤ የሻወር ትሪዎች የእጅ እና የእቃ ማጠቢያ ሲንኮች የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች የውሃና የዘይት ቀለሞች እና ሌሎች የማይንቀሳቀሱ እቃዎችና ያገለገሉ የእጅ መሳሪያዎች እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ህጋዊ የታደሰ ንግድ እና የቫት ተመዝጋቢዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፦

1ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መስቀል ፍላወር መንገድ ድሪምላይነር ሆቴል ጀርባ ወረዳ 02 አይሻ መስጊድ አጠገብ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

2ኛ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ክፍል 7 በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙበትን የጥቅል ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ በማሣየት ድምሩን በእሃዝ ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ተከታታይ 10ኛው የስራ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

3ኛ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤ በጥቅል የመነሻ ዋጋ ከተቀመጠላቸው ዕቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡

4ኛ ተጫራቾች የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ ላይ 5 በመቶ (5%) በማስላት የጨረታ ማስከበሪያ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ ሶስት ጽ/ቤት ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5ኛ የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ክፍት ሲሆን በ10ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡ ፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

6ኛ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

7ኛ የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

8ኛ በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ውል መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታው ማስከበሪያ ለመ/ቤቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

9ኛ አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ በ5 ቀናት በራሳቸው ትራንስፖርት አቅርበው አስጭነው የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡ እቃዎቹን በወቅቱ ካላነሱ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% በየቀኑ እየተሰላ በመቀጫነት እንዲከፈሉ ይደረጋል፡፡ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋ 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡

10ኛ ለሽያጭ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጉድለት የሚገኝ እቃ ካለ ከጠቅላላው መነሻ የዕቃው ነጠላ ዋጋ ለአሸናፊው ተቀናሽ የሚደረግለት ሲሆን ትርፍ ከሆነ በእቃው ነጠላ ዋጋ አሸናፊው ለመውሰድ ፈቃደኛ ከሆነ ይወስዳል፡፡ ገዢ በዚህ ምክንያት ከጎደለው እቃ በከፊልም ሆነ በሙሉ እቃውን ያለመረከብ መብት የለውም፡፡

11ኛ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች:- 09-42-86-88-21/ 09-12-02-29-13 ይደውሉ፡፡

12ኛ ቅርንጫፍ ሶስት ጽ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት

 

Save Tender