Tender Detail

Tender Details


በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (ማሸነሪዎች፣ ትራክተሮች እና ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (ማሸነሪዎች፣ ትራክተሮች እና ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

ሎት -1 ትራክተሮች

ሎት - 2 ማሽነሪዎች

ሎት - 3 ሞተር ሳይክሎች

  • ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና በምሻ ወረዳ ዋስገበታ ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
  • በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
  • ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት 1. ትራክተር ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/፣ ሎት 2 ማሽነሪ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ እና ሎት 3. ሞተር ሳይክል ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም. በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  • የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 16 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  • ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው ቀን/ ከጧቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉ-ትን ተሽከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  • አሸናፊው ተጫራች የተሽከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።
  • ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0913456931/ 0910454656/0916673483/ 0954231528 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender