በደቡብ ኢት/ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ የግብርና ማሽኖችን ለተለያዩ ሥራ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉና የተለያዩ ብረታ ብረት በሚገኙበት ይዞታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2017
በደቡብ ኢት/ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ የግብርና ማሽኖችን ለተለያዩ ሥራ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉና የተለያዩ ብረታ ብረት በሚገኙበት ይዞታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ተሸከርካሪዎች የሚገኙበት አድራሻ ወላይታ ሶዶ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በገጠር ቴክኖሎጅ ማስ/ማዕከል፣ እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል፤ ዳልጋ ከብት ዝሪያ ማሻ/ማዕከል ግብርና ሙ/ሥ ኮሌጅና መንገዶች ባለሥልጣን አ/ምንጭ ልማት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት በአካል በመገኘት ከላይ በኩል በተገለጹት አድራሻ አስቀድመው ማየት እና ሲመለከቱ ከጨረታ ሰነድ ጋር ልዩነት መኖሩን ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመዘጋቱ ከአምስት የሥራ ቀናት በፊት ለአገልግሎቱ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ይህን ሳያደርጉ የቀሩ ተጫራቾች ጨረታው ከታሸገ በኋላ ለሚቀርበው አቤቱታ መ/ቤቱ ምንም ምላሽ ለመስጠት አይገደድም፡፡
- በተሸከርካሪዎች ማሽነሪዎች ጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
- በብረታ ብረት የሚጫረቱ ተጫራቾች በብረታ ብረት ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ይሆናሉ፡፡
- በብረታ ብረት ዘርፍ የሚጫረት ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 100.000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ ብቻ በደቡብ ኢት/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ ስም በማሠራት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ በሚገዙበት የጨረታ መግዣ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በደቡብ ኢ/ክ በፋይናንስ ቢሮ ስም በማቅረብ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታ ማስከበሪያው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- የአሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ጀምሮ አምስት የሥራ ቀን በኋላ ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች CPO ተመላሽ ይደረጋል።
- ስለእሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በቢሮው በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በደ/አ/ክ/መ/ፋይ/ቢሮ አካውንት ቁጥር 1000574914985 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የባንክ ሲሊፑን ይዞ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሀዝና በፈደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፈርማ ማረጋገጥ አለበት ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ ኣይኖርም፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ ማሽነሪ ንብረት ዋጋ በአንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ CPO የተጨመረበት ሁለት በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 15/9/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 6/9/2017 ዓ.ም ዓርብ ዕለት ከቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛው ቀን 6/10/2017 ዓ.ም አርብ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የደረሰ ተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የሌለው እና ተጫራቾች በራሳቸው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው ጨረታውን ከመከፈት እያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ፣ ማሽነሪና ብረታ ብረት ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመከፈል ማንሳት አለባቸው። በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት CPO ለመንግሥት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ ላይ ይውላል፡፡
- መ/ቤቱ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ግልጽ ያደርጋል፡፡
- አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
/ወላይታ ሶዶ/
