የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው የድርጅታችንን ሂሳብ አሰራር በአለም-አቀፍ ፋይናሻል ሪፖርቲንግ ስታንዳርድ/ IRFS በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለሚፈልግ መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናቹ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
Kenema Pharmacy Enterprise (ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክ/ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ54 መድሀኒት ቤቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ/ cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው የድርጅታችንን ሂሳብ አሰራር በአለም-አቀፍ ፋይናሻል ሪፖርቲንግ ስታንዳርድ/ IRFS በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ሰለሚፈልግ መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናቹ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ) ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ንብረት አስ/ጠ/አገ/ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
የስራ ሰአት፡- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር 0118-27-91-23
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
