Tender Detail

Tender Details

  • Company Hilton Addis Ababa (ሒልተን አዲስ አበባ)
  • Address Menelik II Avenue, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011 517 0000
  • Websitehttps://www.hilton.com/en/hotels/addhitw-hilton-addis-ababa/
  • Deadline22 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-27 00:00:00
  • Categories Furniture , Electronics Materials , Used Items , Kitchen Materials

የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ/የተ/የግ ማህበር ንብረትነቱ የልማትና ሆቴል ማህበር (አ.ማ.) የሆኑ የተለያዩ አገልግሎት የሰጡ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Hilton Addis Ababa (ሒልተን አዲስ አበባ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2025

 

የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ/የተ/የግ ማህበር ንብረትነቱ የልማትና ሆቴል ማህበር (አ.ማ.) የሆኑ የተለያዩ አገልግሎት የሰጡ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

- ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ከአዲስ አበባ ሒልተን ኢንተርናሽናል ሂሳብ ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብቻ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡

የዕቃዎቹ አይነቶቹ ዝርዝር፡-

  • የወጥ ቤት መገልገያ ቁሳቁሶች፣
  • የተለያየ መጠንና ቅርፅ ያላቸው ጠረጴዛዎች፣
  • የተለያየ መጠንና ቅርፅ ያላቸው ወንበሮች፣
  • አሮጌና የተለያየ መጠን ያላቸው ቴሌቪዥኖች፣
  • አልጋዎች እና ሌሎችም
  • ለጨረታ የሚቀርብ ማንኛውም ተወዳዳሪ ህጋዊ ፈቃድ ያለው ሆኖ ፈቃዱም በ2017 ዓ. ም. የታደሰ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ዕቃዎች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ ይሁንና ከእያንዳንዱ የዕቃ አይነት በከፈል ነጥሎ መግዛት አይቻልም፡፡
  • ዕቃዎቹን ከግንቦት 11 ቀን እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ብቻ የጨረታ ሰነዱን እየገዙ ማየት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት መነሻ ሰዓት 4፡00 ሰዓት ብቻ በመሆኑ ከ4፡00 ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች እንደማንቀበል በቅድሚያ እናሳውቃለን።
  • ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ግንቦት 15 እና ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ. ም. በሥራ ሰዓት ብቻ ሒልተን አዲስ አበባ ዳይሬክተር ኦፍ ፋይናንስ ቢሮ ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ 10% /አስር በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ ከፍያ ማዘዣ /ሰ.ፒ.አ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲ.ፒ.ኦ ያስቀረበበት እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም /ከጨረታው ውጭ ይሆናል/፡፡
  • ጨረታው ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ በአራት ሰዓት ተኩል (4፡30) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ሒልተን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አሸናፊዎችን ካሳወቅን ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ከፍለው ዕቃውን በሙሉ ማንሳት አለባቸው።

 

ሒልተን አዲስ አበባ

 

Save Tender