በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ስር የሚገኙት ጽ/ቤቶች ሲገለገሉባቸው የነበሩትን ንብረቶች፣ ማለትም ወንበር ፣ ጠረጴዛና ሼልፍ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ስር የሚገኙት ጽ/ቤቶች ሲገለገሉባቸው የነበሩትን ንብረቶች፣ ማለትም ወንበር ፣ ጠረጴዛና ሼልፍ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም፦
- በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የንብረቱን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከፋይናንስና ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት በነፃ በመውሰድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሠነዱን ሞልታችሁ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1231.80 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከ80 ሳንቲም) በባንክ በተረጋገጠ CPO አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ፋ/ጽ/ቤት በሚል ስም ወይም አድራሻ በማሰራት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ አብረው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16 ኛው ቀን 2፡45 ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ቀበና መድሃኒያለም ቤ/ከርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው በወረዳው ወጣት ማዕከል ግቢ ውስጥ በአካል በመምጣት ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጠቅላላ ዋጋው መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በፖስታ ላይ ስም ከነአያት ማንነታቸውን የሚገልጽ የመታወቂያ ኮፒ ስልክ ቁጥር ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን ስም፤ ማህተም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- ዳ/ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ ሳንድፎርድ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-22-28-48 መደወል ይችላሉ፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
