በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የግንባታ ግብዓት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OFWE/MM-002/2017
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የግንባታ ግብዓት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጥቅል መደብ (ሎት) መሠረት እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ሎት አንድ፡- ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /Computers (Desktop. Laptop) እና USP/ እንዲሁም ቀለም ያለቀበት የፕሪንተር ቀለም
- ሎት ሁለት፡- ልዩ ልዩ የቢሮ መሣሪያዎች (ፎቶ ኮፒ ማሽኖች፤ ፕሪንተሮች እና ፋክስ ማሽኖች)
- ሎት ሦስት፡- ልዩ ልዩ ፈርኒቸሮች (የፕላስቲክ ወንበሮች፤ (Managerial and exert chair)፤ የግንባታ ግብዓት (የበር መስታወት)
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሠነዶችን ለእያንዳንዳቸው መደብ (ሎት) የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል / አይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ ለማየት ከፈለጉ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-11:00 ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ምድብ (ሎት) ዋጋ (5%) አምስት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond) በባንክ ክፍያ ማዛዣ (CPO) ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በሚል በማሠራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
