የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 08/2017
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችም፦
- ቧንቧ መገጣጠሚያ
- የተሰፉ ልብሶች
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፓስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ውሃ/አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ/ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም፡፡
- በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ/ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ መ/ቤቱ አይሸፍንም።
- ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ /መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587716840-0587711058፤ 0587711520
ማሳሰቢያ
- የቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎች እና የተሰፉ ልብሶች ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፤ የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃን አይነት እንጅ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መጣችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን፡፡
- ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
የደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
