የኢትዮጵያ ገቢዎት ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለሰራተኞች የሚሆን የታሸገ የመጠጥ ውሃ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በውል ውሃ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገቢዎት ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለሰራተኞች የሚሆን የታሸገ የመጠጥ ውሃ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በውል ውሃ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ መንግስታዊ ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ የተመዘገበ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈለ ሆኖ እነኝህን ማስረጃዎች አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ፡-
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት አራተኛ ፎቅ የግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ (I.S.O) ሰርተፊኬት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብር 60,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 7:30 ታሽጎ በዕለቱ 7፡45 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 7፡30 ሰዓት በፊት የታሸገ ፖስታ በማድረግ አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ
በስልክ ቁጥር 046-220-42-24
046 212-34-68 ይጠቀሙ።
አድራሻ፡- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
