Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline26 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-26 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather , Building Construction , Security Service

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-ኢፕድ 007/2017

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የመጋረጃ አቅርቦት የዕጅ ዋጋን ጨምሮ

ሎት 2 የተለያዩ የህትመት ውጤቶች መሸጫ ኪዮስኮች ግንባታ

ሎት 3 የጥበቃ አገልግሎት

ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ቴክኒክ እና ፋይናንሽያል በ4 በታሸገ ኤንቨሎፖች ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚውል ብር

ለሎት 1. ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ)

ለሎት 2. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)

ለሎት 3. ብር 50,0000.00(ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው፡፡

  1. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በነባሩ ህንጻ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ምድር ላይ ይከፈታል፡፡
  2. ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  3. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69

ኢ.ሜይል procurement@press.et

አድራሻ ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

 

Save Tender