በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ቀጥሎ ያሉትን እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች በየሥራ ዘርፉ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መፈረም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ቀጥሎ ያሉትን እቃዎች
ሎት 1 ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተጓዳኝ እቃዎች
ሎት 2 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች እና የቧንቧ እቃዎች
ሎት 3 የአትክልት እና ፍራፍሬ የላቦራቶሪ እቃዎች
ሎት 4 የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸሮችና ሌሎችም/
ሎት 5 የፕላስቲክና የፕላስቲክ ውጤቶች ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች በየሥራ ዘርፉ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መፈረም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
- በዘርፉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ TIN/ ማቅረብ የሚችሉ ጠ/የግዥ ዋጋ 200,000 ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረበ አለባቸው፡፡
- ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 1% አንድ ፐርሰንት /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 በማስያዝ ፖስታ ውስጥ መረጃውን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሆነ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% የሚያስይዙ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወድድሩ በሎት ስለሆነ በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ዕቃዎች መሞላት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ በአሸነፈው መሰረት ውል ባይወስድ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ከደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ኮፒ በማድረግ ሞልተው በፖስታው ላይ ስማቸውንና ስልክ ቁጥር በመፃፍ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መፃፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ማዕከሉ ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0980216262/0946206131 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል
