የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች ኤሌክትሪክ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 42/2017
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች ኤሌክትሪክ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፤
- ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣፣ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
- ማንኛውም የሞተር ሣይክል ተጫራች ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ መታወቂያ በማቅረብ መጫረት ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6:00: ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11:00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ማንኛውም የሃራጅ ጨረታ ተጫራቾች ለአልባሳትና ጨርቃጨርቅ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ለኤሌክትሪክ ዕቃዎች 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረ CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (ስድስተኛው) ቀን ግልፅ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት በአዲሱ መጋዘን ይካሄዳል፣ የሃራጅ ጨረታው የግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል፣
- ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መገለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፤
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፣
- ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም ፤
- ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 አምስት ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር-0462125396
ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
