Tender Detail

Tender Details


ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2017 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ለትምህርት ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፤ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የስፖርት ትጥቆችን፣ የሕንፃ መሳሪያዎችን እና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስና የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የካቻማሊ መኪና መለዋወጫ፣ ፕላስቲክ የህፃናት መቀመጫ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Hawassa College of Teacher Education (ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)


 

በድጋሚ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2017 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ለትምህርት ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፤ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የስፖርት ትጥቆችን፣ የሕንፃ መሳሪያዎችን እና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስና የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የካቻማሊ መኪና መለዋወጫ፣ ፕላስቲክ የህፃናት መቀመጫ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች:-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የኢፌዲ.ሪ የገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ቀናት በኮሌጁ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ከኮሌጁ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 14 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስልክ ቁጥር 046-221-69-46/046-221-04-87

 

የሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

 

Save Tender