የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮን/መምሪያ ከዲ ኤም ሲ(DMC) እስከ ሴራሚክ ባለ የተለያየ ቦታዎች የህዝብ ሽንት ቤት (Public Toilet) በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮን/መምሪያ ከዲ ኤም ሲ(DMC) እስከ ሴራሚክ ባለ የተለያየ ቦታዎች የህዝብ ሽንት ቤት (Public Toilet) በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ BC-5/Gc-5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው፤
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸዉ፣
- የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሀምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ለሃያ አንድ / ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት በፋይኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ፣ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሠሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራዉ አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ አሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ: አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
