Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች ፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና ኮምፒውተር ዕቃዎች ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ መለዋወጫዎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ቡና እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 12/2017ዓ.ም

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች ፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና ኮምፒውተር ዕቃዎች ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ መለዋወጫዎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ቡና እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አይገደድም/ አያስፈልግም።
  3. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ ግንቦት 06/2017 ዓ.ም ድረስ ለሃራጅ ጨረታ የቀረቡትን ደግሞ እስከ ግንቦት 07/2017 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 መመልከት ይችላሉ፤ 06/2017 ዓ.ም ድረስ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 06/2017 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ።
  5. የግልፅ ጨረታው ግንቦት 07/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ግንቦት 07/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  8. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፣
  9. የሃራጅ ጨረታው ግንቦት 07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፤
  11. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5 /በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ከላይ በተ/ቁ 11 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
  13. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም፤
  14. ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፤
  15. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት እቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  16. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058-320-74-18/058-320-75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender