Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር
  • Address ጎጃም በረንዳ ሀግቤስ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0917 80 42 41
  • Website
  • Deadline17 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-17 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር በስሩ የሚገኙትን ፕሮጀክቶች የሂሳብ አዲት ለሶስት ተከታታይ አመት የሚቆይ ኮንትራት ገብቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ቁጥር ኢ/ወ/አ/ቤ/ክ/ህ/ወ/መ/ማህበር 055/2017 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር በስሩ የሚገኙትን ፕሮጀክቶች የሂሳብ አዲት ለሶስት ተከታታይ አመት የሚቆይ ኮንትራት ገብቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ጨረታውን መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ቲን እና ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጎጃም በረንዳ ሀግቤስ ፊት ለፊት የሚገኘው የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና በመስሪያ ቤታችን ስም ማለትም የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በመፈረም እና ህጋዊ ማህተም ማድረግ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በተለያየ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በጠቀስነው አድራሻ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊ ድርጅቱ ባሸነፈበት ዋጋ 10 በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊነቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለበት፡፡
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0917 80 42 41 / 0917 80 07 97 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ወንጌል አርነት የህጻናት ወጣቶች መርጃ ማህበር

Save Tender