Tender Detail

Tender Details

  • Company Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ወርቁ ሰፈር (ውሃ ልማት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ መስጊዱ እካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 17 51 51
  • Websitehttps://www.dce-et.com/
  • Deadline20 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-20 00:00:00
  • Categories Construction Equipment And Machinery , Machinery , Metals And Metal Working , Vehicle

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ ቀደም ሲገለገልባቸው የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች፣ ማሸነሪዎች፤ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxillary Equipments) እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በእስክራፕ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እና ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxillary Equipments) በቁርጥራጭ ብረትነት ለመሸጥ የተዘጋጀ የሽያጭ ሰነድ ጨረታ ቁጥር ንብ/001/2017

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ ቀደም ሲገለገልባቸው የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች፣ ማሸነሪዎች፤ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxillary Equipments) እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በእስክራፕ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ሊያሟላቸው የሚገቡ የቅድመ ሁኔታ (ህጋዊነት ያላቸው ሰነዶች)
    1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት (trading liscense) (12017 የታደሰ)
    2. የታክስ ከፋይ ሰርተፍኬት (Tax Payer Identification Certificate)
    3. የብረታ ብረት ማቅለጫ ድርጅት መሆኑን ወይም በዘርፉ መሰማራታቸውን የሚያረጋግጥ ንግድ ፍቃድ
    4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዘገባ ሰርተፍኬት (Value Added Tax Registration Certificate)
    5. ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance)
    6. በየትኛውም የመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ (debar) ስለመሆናቸው ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ Online ማቅረብ አለባቸው።
    7. ከባለቤት እና ከሥራ አስኪያጅ ውጪ ተወካይ ከሆነ ተቀባይነት ያለው የስልጣን ውክልና (Power of attorney)
    8. ተቀባይነት ያለው የጨረታ ማስከበሪያ
    1. የተፈረመ የተጫራቾች ያለማጭበርበር ቃል የገቡበት ቅጽ
  1. ተጫራቾች የ2016 ዓ ም በኦዲተር የተመረመረ የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች ለዚህ ጨረታ ብቁ የሚሆነው 2016 ዓመታዊ ገቢው (annual turover) ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ነው።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምሥት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 6፡00 ባሉት የሥራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪና ማሽነሪ ብረቶች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሚ 6፡00 ሰዓት ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት ከ3:00 እስከ 6:30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11:00 ሰዓት ቃሊቲ ግቢ (ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ እና ወርቁ ሰፈር) በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ቢያንስ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ኪ.ግ ቁርጥራጭ ብረቶች ለአሸነፈበት ዋጋ ውል አስሮ ከፍያ በመፈፀም የመውሰድ አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በጥቅል ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) በድርጅታችን ትክክለኛ ስም “መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሚል አሰርተው ሲፒኦውን ከኦርጅናል ቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዱ ጋር አልያም ለብቻው በሌላ ፖስታ በማሸግና ሲፒኦ ብሎ በመጻፍ የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ በ4፡15 (አራት ሰዓት ከሩብ) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

ስልክ ቁጥር 011-4-40-34-34

ማዞሪያ 011-4-42-2270/71/72

E-MAIL አድራሻ Info @dce-et.com

የድህረ ገፅ አድራሻ WWW.dce-et.com

ፖስታ ሣ.ቁጥር፡- 3414 114-40-04-71/0114-42-07-46

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender