Tender Detail

Tender Details


ድርጅታችን ወርልድቪዥን ኢትዮጵያ የተለያየ ብዛት ያላቸውን ያገለገሉ የቶዮታ ተሽከርካሪዎች፣ ጎማ እና መለዋወጫዎች፣ የሞተር ብስክሌቶች፣ ጀነሬተሮች፣ የውሃ ስራ እቃዎች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ኮምፒውተሮች እና መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

World Vision Ethiopia (ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ)


 

ያገለገሉ የቶዮታ ተሽከርካሪዎች፣ ጎማ እና መለዋወጫዎች፣ የሞተር ብስክሌቶች፣ ጀነሬተሮች፣ የውሃ ስራ እቃዎች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ኮምፒውተሮች እና መለዋወጫዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2017

 

ድርጅታችን ወርልድቪዥን ኢትዮጵያ የተለያየ ብዛት ያላቸውን ያገለገሉ የቶዮታ ተሽከርካሪዎች፣ ጎማ እና መለዋወጫዎች፣ የሞተር ብስክሌቶች፣ ጀነሬተሮች፣ የውሃ ስራ እቃዎች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ኮምፒውተሮች እና መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።

  1. የጨረታ ዶከመንት ለመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ ብር) ብቻ በመክፈል ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ከግንቦት 6-8 ቀን 2017 ዓ.ም በስራ ሰዓት የሚሸጡትን የቶዮታ ተሽከርካሪዎች፣ ጎማ እና መለዋወጫዎች፣ የሞተር ብስክሌቶች፣ ጀነሬተሮች፣ የውሃ ስራ እቃዎች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ኮምፒውተሮች እና መለዋወጫዎችን በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት እና ጥያ ከተማ ከኖክ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ ቢሮ ቅጥር ግቢ በመቅረብ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት መለዋወጫዎች የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከግንቦት 11-13 ቀን 2017 ዓ.ም. የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ [ሎት] የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20% በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ስም በባንኩ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ [ሲፒኦ] ከጨረታው ሰነድ ጋር ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በተጫራቾች ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያውኑ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት [ሲፒኦ] ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታ አሸንፈው ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጨረታ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ የሚመለስላቸው ይሆናል።
  8. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ገርጂ አንበሳ ጋራዥ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 0116293350/55/56/57 - 0911-015979 ፖ.ሳ.ቁ. 3330, አዲስ አበባ

 

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ

 

Save Tender