የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር PPS/NVP-3FBI/08/09/2017
የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የብረታ ብረቶቹን ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስቀረውም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ብረታ ብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ20 የስራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡ ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትክክለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የሰጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ20 (ሀያ) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 13 78 56 06 ወይም 0912034552 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡
የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት
