ቂርቆስ የገበያ ማዕከል አክስዮን ማህበር የገበያ ማዕከሉን ህንጻ ህጋዊ በሆኑ ተጫራቾች ማቴሪያል በራሳቸው በማቅረብ የውጪ ሸክላና የግድግዳ ቀለም ቅብ ስራ፣ የደረጃና የኮሪደሮች ብረት/ hand rail/ የዝገት መከላከያና ቀለም ቅብ ስራ፣ የኮለን እና የቢም ቀለም ቅብ ስራ፣ የጣራ ገተር እና ውሃ መውረጃ /አሸንዳ ጥገና ስራ፣ የጣራ ቆርቆሮ ቀለም ቅብ ስራ እንዲሁም ጠቅላላ የቀለም ቅብ ስራ እድሳት በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
የቂርቆስ የገበያ ማዕከል አክስዮን ማህበር
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
ቂርቆስ የገበያ ማዕከል አክስዮን ማህበር የገበያ ማዕከሉን ህንጻ ህጋዊ በሆኑ ተጫራቾች ማቴሪያል በራሳቸው በማቅረብ የውጪ ሸክላና የግድግዳ ቀለም ቅብ ስራ፣ የደረጃና የኮሪደሮች ብረት/ hand rail/ የዝገት መከላከያና ቀለም ቅብ ስራ፣ የኮለን እና የቢም ቀለም ቅብ ስራ፣ የጣራ ገተር እና ውሃ መውረጃ /አሸንዳ ጥገና ስራ፣ የጣራ ቆርቆሮ ቀለም ቅብ ስራ እንዲሁም ጠቅላላ የቀለም ቅብ ስራ እድሳት በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ለስራው ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ የ2017 ዓ ም በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል
- ተጫራቾች የስራውን ዝርዘር በአካል ቀርበው በማየት በተዘጋጀው የጨረታ መሙያ/ BOQ (Build Own Oprate) ሰነድ ላይ በአግባቡ ሙላት አለባቸው
- ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃቸው GC/BC 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ስራ ተቋራጮች
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውል ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋው 2% በተረጋገጠ የባንክ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል
- ሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈጻሚው አካል የበላይ ኃላፊ ወይም ከህጋዊ ውክልና ውጭ በተጫራቾች የሚቀርብ ከሆነና የመጫረቻ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ ሰነዶች ለየብቻቸው ታሽገው መቅረብ አለባቸው በተጨማሪም ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ለብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው ከአክሲዮኑ ቢሮ ቁጥር A-313 መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቂርቆስ የገበያ ማዕከል አክስዮን ማህበር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር A-312 በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር +251 11 416 0515 /09 04 61 68 85 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር A-311- A-313 ልዩ ቦታው ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት
የቂርቆስ የገበያ ማዕከል አክስዮን ማህበር
