Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ከታህሳስ ወር 2008 ዓ.ም የተቋቋመና በመንግስት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት የሚተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን ከኮርፖሬሽኑ ዘርፎች አንዱ የሆነው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ሳሪስ እና ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ በሚድሮክ ገባ ብሎ በሚገኙ ይዞታዎቹ የሚገኙ ያገለገሉ ቆርቆሮዎች፣ የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ባለክርና ባለሽቦ ጎማዎች ፣ ተንቀሳቃሽ የማይሰሩ እና የሚሰሩ ሚዛኖች። የተለያዩ በርሜሎች፣ ጀነሬተር፣ ክሪከ፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ፕሬዠር ማሽን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


 

ያገለገሉ ብረታ ብረት፣ ተንቀሳቃሽ ሚዛኖች ፤ንቃይ

ቆርቆሮዎች እና የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ከታህሳስ ወር 2008 ዓ.ም የተቋቋመና በመንግስት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት የሚተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን ከኮርፖሬሽኑ ዘርፎች አንዱ የሆነው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ሳሪስ እና ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ በሚድሮክ ገባ ብሎ በሚገኙ ይዞታዎቹ የሚገኙ ያገለገሉ ቆርቆሮዎች፣ የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ባለክርና ባለሽቦ ጎማዎች ፣ ተንቀሳቃሽ የማይሰሩ እና የሚሰሩ ሚዛኖች። የተለያዩ በርሜሎች፣ ጀነሬተር፣ ክሪከ፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ፕሬዠር ማሽን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም፡-

  1. ተጫራጮች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፤
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  3. ተጫራጮች ጨረታው አየር ላይ በሚውልባቸው ቀናት ሳሪስ ሚቸል ኮትስ እና ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ በሚድሮክ ገባ ብሎ በሚገኙ የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አቃ/ቃሊ/ክ/ከተማ ወረዳ 05 ከማሰልጠኛ ከፍ ብሎ የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የዘርፉ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይቻላል፤
  5. ተጫራቾች በከፊል ወይም በተናጠል መግዛት ይችላሉ፤ ሁሉንም ዕቃዎች በመመልከት በጥቅል ወይም በተናጠል የሚገዙበትን ዋጋ በመግለጽ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ ቃሊቲ የዘርፉ ዋና መ/ቤት ለዚሁ በሚዘጋጅ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  6. የጉልበት ሰራተኞች እና የጭነት ተሽከርካሪ ክፍያዎች በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፣
  7. ጨረታው በ15ኛው ቀን (በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን) ከቀኑ 9፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ 9፡30 የጨረታ ሣጥኑ ይከፈታል፤
  8. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 53 84 58 11/0114622767 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender