አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል UPS ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈፀም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ፑል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል UPS ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈፀም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
የተጫራቾች መመሪያ
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- ተጫራቾች 200,000.00 በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ)፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል፣ ኦርጅናልና ኮፒ፣ ፋይናሽያል ኦርጅናል ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ኦርጅናል የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለባችሁ፤
- የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት ተጨማሪ እሴት ሰርቲፊኬት የሚነበብና የሚታይ መሆን አለበት፣
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በግዥ ፋይ ንብ/አስ/ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር L-12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጉ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር L-12 በግልፅ ይከፈታል። በዚህ ቀን ያልተገኙ ተጫራቾች የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉሉም፡፡ ነገር ግን 16 ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር L -12 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ መጠየቅ (መረጃ መላክ ይችላሉ) ይችላሉ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጥር 058-220-79-40/058-22614-39
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ፑል
/ባህር ዳር/
