Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Seed Enterprise (የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ሕንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-416 03 09
  • Websitehttps://oromiaseedenterprise.com/
  • Deadline16 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-16 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Stationery Materials , Vehicle tire , Machinery Spare Parts

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ሎት1 የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 2 የቢሮ ዕቃዎች ሎት3 ቶነሮች (የኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች) እና ሎት4 የመኪና ጎማዎች እና የውስጥ ላስቲክ (ከነመዳሪ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Oromia Seed Enterprise (የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ)


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OSE/NCB/016/2017

 

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ሎት1 የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 2 የቢሮ ዕቃዎች ሎት3 ቶነሮች (የኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች) እና ሎት4 የመኪና ጎማዎች እና የውስጥ ላስቲክ (ከነመዳሪ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን

ተጫራቾች፡-

  1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
  2. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
  5. የአቅራቢነት ማስረጃ (Suppliers List)
  6. የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን ፤ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንዳድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡

የጨረታ ሳጥኑ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡

ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፤

ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 011-416 03 09/011-466-25-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

Save Tender