Tender Detail

Tender Details

  • Company ተስፋዬ ተሰማ ሺበሺ የተመሠከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት ኦዲተር (የሒሳብ አጣሪ)
  • Address ከአፍሪካ ሕብረት ሚካዔል በስተግራ ካለው ሶስተኛ ቅያስ ከይሚ ሬስቶራንት በስተቀኝ ከሚገኘው ባለሰማያዊ ቀለም ቅብ ሕንጻ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር ብሎክ 3/403 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-11-42-90-35
  • Website
  • Deadline02 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-02 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Machines And Computers , Stationery Materials , Construction Machinery , Cargo Vehicle

በመጣራት ላይ ያለው ድርጅት በይዞታው የሚገኙትን፡- የእቃ መጫኛ መኪና፤ የግራናይት መቁረጫና ቅርፅ ማውጫ ማሽኖች፤ የቢሮ ጠረጴዛና ወንበሮች፤ ኮምፒውተርና ፕሪንተሮች፤ ካዝና፤ የውሃ ማጣሪያና 500 ሚ.ሊ ሮቶ፤ ሼልፍ፤ ወረቀት መብሻ፤ ስቴፕለር የመሳሰሉትን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተስፋዬ ተሰማ ሺበሺ የተመሠከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት ኦዲተር (የሒሳብ አጣሪ)


 

በመጣራት ላይ ያለውን የይብራዛ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማ

ንብረት ማስወገድ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 04/የት/2017

 

በመጣራት ላይ ያለው ድርጅት በይዞታው የሚገኙትን፡- የእቃ መጫኛ መኪና፤ የግራናይት መቁረጫና ቅርፅ ማውጫ ማሽኖች፤ የቢሮ ጠረጴዛና ወንበሮች፤ ኮምፒውተርና ፕሪንተሮች፤ ካዝና፤ የውሃ ማጣሪያና 500 ሚ.ሊ ሮቶ፤ ሼልፍ፤ ወረቀት መብሻ፤ ስቴፕለር የመሳሰሉትን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከገዛ በኋላ በጨረታ ሰነዱ በሚገለፀው ጎተራ በሚገኘው መጋዘን ለጨረታ የተዘጋጁትን እቃዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት የሥራ ቀኖች ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ።

        1. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን ዕቃዎች በዝርዝር የያዘ ሰነድ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በአካል በመገኘት በብር 200 ሰነዱን በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
        2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ-አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀኖች ከ4፡00 ሰዓት በአጣሪው አድራሻ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ይህ የጨረታ መነሻና መዝጊያ ቀን በጨረታ ሰነዱ በማያሻማ ሁኔታ የሚገለፅ ይሆናል።
        3. በጨረታ ለመሳተፍ እያንዳንዱ ተጫራች የብር 10,000 (አስር ሺህ) ሲፒኦ በሚጣራው ድርጅት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
        4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሱት ለሚፈልጉት ንብረት ብቻ ለይተው መወዳደር ይችላሉ።
        5. ለአንዱ ጨረታ ዓይነት ለውድድር የሚቀርበው ተጫራች ቁጥር ከ3 ሰው ሲያንስ አጫራቾች ውድድሩን የመሰረዝ፤ ድጋሚ ጨረታ የማውጣት ወይም ባለው እንዲወሰን የማድረግ መብታቸው የተጠበቀ ነው።
        6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው አምስተኛ የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአጣሪው ይከፈታል።
        7. አሸናፊ ላልሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
        8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘና አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ የጨረታ ጊዜ ገደቡን የማራዘም መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከአፍሪካ ሕብረት ሚካዔል በስተግራ ካለው ሶስተኛ ቅያስ ከይሚ ሬስቶራንት በስተቀኝ ከሚገኘው ባለሰማያዊ ቀለም ቅብ ሕንጻ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር ብሎክ 3/403 2ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር፡- 09-11-42-90-35/011-5-58-63-77 ይደውሉ።

 

ተስፋዬ ተሰማ ሺበሺ የተመሠከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት ኦዲተር (የሒሳብ አጣሪ)

 

Save Tender