በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ፣ ለግንባታ፣ ለማሰልጠኛ፣ ለብቃት ምዘና ማስመዘኛ እና ለተለያዩ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
St.Lalibela Poly Technic College (የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ፣ ለግንባታ፣ ለማሰልጠኛ፣ ለብቃት ምዘና ማስመዘኛ እና ለተለያዩ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን እቃዎች፡-
|
ምድብ |
የንግድ ስራ መስክ |
|
ሎት 1 |
ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ችርቻሮ ንግድ |
|
ሎት 2 |
ኮምፒዩተር፣ የኮምፒዩተር መሳሪያዎችና ተጓዳኝ እቃዎች ችርቻሮ ንግድ |
|
ሎት 3 |
የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ችርቻሮ ንግድ |
|
ሎት 4 |
የኤልክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች ችርቻሮ ንግድ |
|
ሎት 5 |
ሱፐር ማርኬት |
|
ሎት 6 |
አትክልትና ፍራፍሬ (የተዘጋጁትንም ጨምሮ) ምርቶች ችርቻሮ ንግድ |
|
ሎት 7 |
የህትመት ተዛማጅና ስራዎች (የባጅ ስራ) |
|
ሎት 8 |
የመጠጥ ችርቻሮ ንግድ |
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች እና ጠቅላላ የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በየምድቡ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ዋጋው ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን የብር መጠን በጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያው በወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ3፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይተላለፋል።
- የሚገዙ የእቃዎችንና አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-3-36-10-13 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የቅዱስ ላሊበላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
