Tender Detail

Tender Details

  • Company የአሳሳ ዶዶላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0939107001
  • Website
  • Deadline06 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-06 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአሳሳ ዶዶላ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የአሳሳ ዶዶላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአሳሳ ዶዶላ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል

  • የሰራተኛ የደንብ ልብሶች (ሎት1)
  • የጽህፈት መሳሪያዎች (ሎት2)
  • የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት3) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
  1. ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን የ2017 ያደሱ መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ 1% ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከአሳሳ ዶዶላ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ክፍል በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን (ቴክኒክና ፋይናንሻል ለየብቻ) በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ) ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድርጅት በፅሁፍ ከተገለፀ በኋላ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ በአሳሳ ዶዶላ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. የእቃዎች ርክክብ የሚካሄደው በአሳሳ ዶዶላ ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡
  11. የእቃው ብዛት (Quantity) የሚወሰነው በመስሪያ ቤቱ (ድርጅቱ) የበጀት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ከበጀታችን በላይ የሚሆነውን መቀነስ ወይም መጨመር የምንችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አድራሻ፡- አሳሳ ስልክ 0939107001/0912254219

 

የአሳሳ ዶዶላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender