Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ ፣ የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እና ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 40/2017

 

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ ፣ የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እና ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው ያላት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
  2. ማንኛውም የሞተር ሣይክል ተጫራች ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ መታወቂያ በማቅረብ መጫረት ይችላል፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፤ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ /በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  5. የሃራጅ ጨረታ ተጫራቾች ለአልባሳትና ጨርቃጨርቅ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን በ6ኛው (ስድስተኛው) ቀን ግልፅ ጨረታው በ4፡00 ሰዓት በአዲሱ መጋዘን ይካሄዳል፡ የሃራጅ ጨረታው የግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ ይካሄዳል፣ ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል፡፡
  7. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  10. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  12. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው::
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
  14. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-53-96

 

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender