ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል::
Ethio Life and General Insurance S.C (ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ)
የጨረታ ቁጥር ELiG/07/2026
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | ሎት | አይነት | መለያ |
| 1 | ሎት 1 | የፋይል ማስቀመጫ ቁም ሳጥን | የቢሮ ፋይሎች ማስቀመጫ ቁም ሳጥን ግድግዳ ላይ ሚገጠም |
| 2 | ሎት 2 | የመኪና ጎማ | የአውቶሞቢል እና ፒክአፕ |
በጨረታው ለመሳተፍ:-
- ተጫራቾች ከላይ ከተገለፁት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ በሁሉም ወይም በተናጠል መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ስም በሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት መስቀል ፍላወር በሚገኘው የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት "ሆም ኦፍ ሚሊዮንስ" ህንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በዚሁ ቀን ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ በኩባንያው የስልጠና አዳራሽ 8ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4702077 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት
መስቀል ፍላወር ሆምስ ኦፍ ሚሊዮንስ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ
ስልክ 011-4702077/0115570606
✨ messages.ai_summary
Supply of office file cabinets for wall mounting (Lot 1) and vehicle tyres for automobiles and pickups (Lot 2) for Ethio Life and General Insurance. Bidders may bid for all or individual lots; valid trade registration certificate, trade licence, tax clearance and VAT certificate required.
