የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮንስ/መምሪያ በበጀት ዓመቱ ቢሮን ለማስጠገን በታቀደው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም እንዲቻል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው ማህበር መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ልማት መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮንስ/መምሪያ በበጀት ዓመቱ ቢሮን ለማስጠገን በታቀደው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም እንዲቻል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው ማህበር መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በኮንስትራከሽን ዘርፍ የተሰማሩ፤
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ለሃያ እንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ በብር 500 (አምስት መቶ) ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት ምድብ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ አ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ እንድ አሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር-046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
